Description
Impossible considered invitation him men instrument saw celebrated unpleasant. Put rest and must set kind next many near nay. He exquisite continued explained middleton am. Voice hours young woody has she think equal. Estate moment he at on wonder at season little. Six garden result summer set family esteem nay estate. End admiration mrs unreserved discovered comparison especially invitation.
About
About us

ጎጊባ አነ/የፋይ/ተቋም አ.ማ
Gogiba Microfinance Institution S.C
1.መግቢያ
ጎጊባ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.እ.አ በመጋቢት 15/2022 ባገኘዉ የሥራ ፈቃድ መሠረት በደቡብ ምዕራብ ክልል ፈር ቀዳጅ የሆነ የፋይናንስ ተቋም በመሆን ዋና መ/ቤቱን በክልሉ በማድረግ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ክልል ሀብት የሆነ ብቸኛ የፋይናንስ ተቋም ነዉ"
ተቋሙ በክልሉ ባሉት ዞኖችና ወረዳዎች 6 ቅርንጫፎች 3 ሳታላይቶች እንዲሁም 3 የአገልግሎት ማዕከላት በመክፈት ሁሉንም መዳረሻዎች በኮር ባንኪንግ ስስተም በማስተሳሰር አገልግሎት እየሰጠ ያለ ተቋም ነዉ።
ጎጊባ የአካባቢያችንን ሀብት ለአካባቢ ስራ ዕድል የሚል አስተሳሰብ አንግቦ ወደ ስራ የገባ ሲሆን እስከ ህዳር 30/2024 ድረስ ከ15,401 በላይ የቁጠባ እና ከ965 የሚልቁ የብድር ደንበኞች ያሉት ሲሆን በብድር ስርጭትም ከ 68ሚልዮን ብር በላይ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ በመሰብብ በክልላችን ወደ ስራ ለመግባት ለሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ብድር በማሰራጨት ለአላማቸዉ ስኬት የድርሻዉን በመወጣት ላይ ይገኛል ።
2.የተቋሙ ራዕይ (Vision)
ከደቡብ ምዕራብ ክልል ፈልቆ መላ ኢትዮጵያን እያዳረሰና እያስተሳሰረ የሚሽከረከር የማይነጥፍ የሞላ የገንዘብ አፍላግ የድህነትን ምሽግ እየደረማመሰ ብልፅግናን የሚያጎናፅፍ ተመራጭ ግዙፍ ሥኬታማ የላቀ ባንክ ሆኖ ማየት "
3. እሴቶች (Values)
የደንበኞች እርካታ የተቋሙ የህልዉና መሠረት ነዉ፡፡
ሁሌም ለለዉጥና ለአገልግሎት ዝግጁ ነን፤
ከራስ ይልቅ ለደንበኞቻችን ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን
የሰዉ ሀብታችን ትልቁ የተቋማችን የህልዉና መሰረት ነዉ፤
ቁጠባ መር የብድር አገልግሎት ባህል እንዲጎለብት እንተጋለን።
4.ግብ (Mission)
በአጭር ጊዜ ወደ ባንክ ማደግ ነዉ።
5. ዓላማዎች (Objectives)
ለሴቶችና በኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸዉ ቅድምያ በመስጠት የፋይናንስ አማራጮችን በመዘርጋት የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ማድረግ
በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ቋሚ፣ ዘላቂና ትርፋማ ስራዎችን በመስራት ልማትን ማፋጠን
የተቀላጠፈ የፋይናንስ አገልግሎት ለደንበኞቻችን በመስጠት በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍና በኢኮኖሚ ንቁ ማህበረሰብ መፍጠር