ጎጊባ አነ/የፋይ/ተቋም አ.ማ

About

About us

ጎጊባ አነ/የፋይ/ተቋም አ.ማ
Gogiba Microfinance Institution S.C
1.መግቢያ
ጎጊባ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.እ.አ በመጋቢት 15/2022 ባገኘዉ የሥራ ፈቃድ መሠረት በደቡብ ምዕራብ ክልል ፈር ቀዳጅ የሆነ የፋይናንስ ተቋም በመሆን ዋና መ/ቤቱን በክልሉ በማድረግ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ክልል ሀብት የሆነ ብቸኛ የፋይናንስ ተቋም ነዉ"
ተቋሙ በክልሉ ባሉት ዞኖችና ወረዳዎች 6 ቅርንጫፎች 3 ሳታላይቶች እንዲሁም 3 የአገልግሎት ማዕከላት በመክፈት ሁሉንም መዳረሻዎች በኮር ባንኪንግ ስስተም በማስተሳሰር አገልግሎት እየሰጠ ያለ ተቋም ነዉ።
ጎጊባ የአካባቢያችንን ሀብት ለአካባቢ ስራ ዕድል የሚል አስተሳሰብ አንግቦ ወደ ስራ የገባ ሲሆን እስከ ህዳር 30/2024 ድረስ ከ15,401 በላይ የቁጠባ እና ከ965 የሚልቁ የብድር ደንበኞች ያሉት ሲሆን በብድር ስርጭትም ከ 68ሚልዮን ብር በላይ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ በመሰብብ በክልላችን ወደ ስራ ለመግባት ለሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ብድር በማሰራጨት ለአላማቸዉ ስኬት የድርሻዉን በመወጣት ላይ ይገኛል ።
 

2.የተቋሙ ራዕይ (Vision)
ከደቡብ ምዕራብ ክልል ፈልቆ መላ ኢትዮጵያን እያዳረሰና እያስተሳሰረ የሚሽከረከር የማይነጥፍ የሞላ የገንዘብ አፍላግ የድህነትን ምሽግ እየደረማመሰ ብልፅግናን የሚያጎናፅፍ ተመራጭ ግዙፍ ሥኬታማ የላቀ ባንክ ሆኖ ማየት "
 

3. እሴቶች (Values)
    የደንበኞች እርካታ የተቋሙ የህልዉና መሠረት ነዉ፡፡
    ሁሌም ለለዉጥና ለአገልግሎት ዝግጁ ነን፤
    ከራስ ይልቅ ለደንበኞቻችን ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንሰጣለን
    የሰዉ ሀብታችን ትልቁ የተቋማችን የህልዉና መሰረት ነዉ፤ 
    ቁጠባ መር የብድር አገልግሎት ባህል እንዲጎለብት እንተጋለን።
 

 

 4.ግብ (Mission)
    በአጭር ጊዜ ወደ ባንክ ማደግ ነዉ።
 

 

 

5. ዓላማዎች (Objectives)
    ለሴቶችና በኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸዉ ቅድምያ በመስጠት የፋይናንስ አማራጮችን በመዘርጋት የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ማድረግ
    በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ቋሚ፣ ዘላቂና ትርፋማ ስራዎችን በመስራት ልማትን ማፋጠን 
    የተቀላጠፈ የፋይናንስ አገልግሎት ለደንበኞቻችን በመስጠት በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍና በኢኮኖሚ ንቁ ማህበረሰብ መፍጠር
 

 

Learn more